Wednesday, August 6, 2014

ፍትህ ምኒስቴር አምስት የግል መጽሄቶችን እና አንድ ጋዜጣን ህገመንግስቱን በሃይል ለመናድ ሞክረዋል በማለት ከሰሰ

Lomi magazine, Enque magazine, Fact magazine, Jano magazine, Lomi magazine, and Afro-Times newspaperምንስቴሩ ከትላንት በስትያ መንግስት በሚቆጣጠረው የቴሌቪዥን ማሰረጫ ባወጣው የተድበሰበሰ መግለጫ፡ እነዚህን የግል መጽሄቶችን፡ ጋዜጣውን እና አሳታሚዎቻቸውን «ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን በአመጽ ለመናድ…» በሚል ክስ የመሰረተባቸው ሲሆን ጋዜጠኞቹ እስካሁን የክስ መጥሪያ እንዳልደረሳቸውና መከሰሳቸውን እንደማንኛውም ሰው የሰሙት በቴሌቪዥን መሆኑን እየተናገሩ ነው፡፡ አቃቤ ህግ «ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን በአመጽ ለመናድ፡ ህዝብን ለዓመጽ ለማነሳሳት እና በመንግስት ላይ እምነት እንዲያጣ ያደርጋሉ» ብሎ የከሰሳቸው የግል መጽሄቶች እና ጋዜጣው የሚከተሉት ናቸው። 
1ኛ ሳምንታዊው አዲስ ጉዳይ መጽሄት፡ እና ሮዝ የግል አሳታሚ ድርጅት 
2ኛ ሳምንታዊው ሎሚ መጽሄት፡ እና ዳዲሞስ የግል አሳታሚ ድርጅት 
3ኛ በሳምንት ሁለት ጊዜ የሚታተመው እንቁ እና አለማየሁ የግል አሳታሚ ድርጅት 
4ኛ ሳምንታዊ ፋክት መጽሄት እና ዮፋ የግል አሳታሚ ድርጅት 
5ኛ በሳምንት ሁለት ጊዜ የሚታተመው ጃኖ መጽሄት እና አስናቀ የግል አሳታሚ ድርጅት ሲሆኑ 
ስደስተኛው እና በቅርብ ጊዜ መታተም የጀመረው አፍሮ ታይምስ የተባለው ሳምንታዊ ጋዜጣ የሎሚ መጽሄት አጋር እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል። 
ይህ በእንዲህ እንዳለ፡ጠቅላይ ምኒስትራችን አሜሪካን አገር በተካሄደው የአፍሮ አሜሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ መንግስታቸው ከምንግዜውም በበለጠ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ቁርጠኝነቱን ለፕሬዚዳንት ኦባማ እና ለተሰብሳቢዎች ገልጸዋል። ሽብርተኞቹ የተባሉት እንግዲህ፡ በማእከላዊ፡በቃሊቲ፡በቂሊንጦ፡በዝዋይ እና በሌሎች እስርቤቶች ባልሰሩት ወንጀሎች ተይዘው ክስ ሳይመሰርትባቸው ወይም በሃሰት ተወንጅለው የሚሰቃዩት የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች፡ጋዜጠኞች፡የሲቪል ተቋማት መሪዎች፡የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እና ተከታዮቻቸው፡ እና ሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ መሳሪያ ያልጨበጡ ኢትዮጵያውያን የጸረሽብረተኛ ህጉ ሰለባዎች ናቸው።

ምንጭ ኢሬቴድ

No comments:

Post a Comment